በአማራ ክልል ከታህሳስ 24 ቀን 2017 ዐ/ም ጀምሮ ዳግመኛ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 238 ሰዎች ሲያዙ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጷል።
በክልሉ የተከሰተው ወረርሽኝ በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ላይ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ወረርሽኙ በመስፋፋት በጎንደር ፣በባህርዳር፣በገንደውሀ ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከተማ ላይ መከሰቱን በኢንስቲትዩቱ የበሽታዎችና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አሰጣጥ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ ተናግረዋል ፡፡
የኮሌራ ወረርሽኙ በድጋሚ ታሕሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተ መሆኑን ያነሱት ሲስተር ሰፊ ደርብ ከታሕሳስ 24 እስከ የካቲት 5 ባሉ ጊዜያት ብቻ 238 የሚሆኑ ዜጎች በወረርሽኝ መያዛቸውን አስታውቀዋል ፡፡
በተጨማሪም በወረርሽኙ ምክንያት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነግረውናል ፡፡
ወረርሽኙ እንዳይዛመት ህመምተኞች በተገኙበት የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ክሎሪን በመርጨት የብክለት መከላከል ስራዎች በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል እየተሰራ መሆኑ ተነስቶል ፡፡
የአደጋ ስጋት ተግባቦት የጤና ትምህርት በተከሰተባቸው እና በተስፋፋባቸው አካባቢዎች በመስጠት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተነግሮል ፡፡
የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
Related News
23 Apr, 2025
Rory McIlroy to return to action at Zuri . . .
30 Jun, 2025
"Until Virat Kohli and Rohit Sharma were . . .
24 Jun, 2025
Elizabeth Hurley's new boyfriend Billy R . . .
18 Jun, 2025
Liverpool to begin Premier League title . . .
12 Apr, 2025
Giants vs. Yankees prediction, odds, pic . . .
17 Aug, 2025
Campaigns pick up pace as DUSU polls dra . . .
04 Jun, 2025
LA 2028 unveils Paralympics venue plan
06 Jun, 2025
Pilgrims stone the devil as Haj nears en . . .